በመጽሐፉ መረቃ ስነስርዓት ላይ የታደሙት የድሬዳዋ አስተዳር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ድሬዳዋ የኪነትና ከያኒያን መፍለቂያነቷ የማይነጥፍ ነው ብለዋል ፡፡
“ ሒጋ “ በሚል ርእስ በኢንጂነር ነስረዲን ሐሰን በአፋን ኦሮሞ ተጽፎ ለአንባቢያን የቀረበው ይሕ መጽሃፍ በሃያ አንድ ምእራፎች ተደራጅቶ በሶስት መቶ ሰባ ገጾች የተዘጋጀ ሲሆን ከተፈጥሮ ተነስቶ ህዋና ምህዋሯን እስከ ፕላኔቶች የዘለቀ የሃሳባት ጥግ የሚጓዝ መሆኑን በምረቃ መድረኩ ላይ ተወስቷል ፡፡
ከዚህመ ባሻገር በዓለም ታላቅ ተጽእኖ አሳርፈዋል ያላቸውን አምስት ሰዎችን ደራሲው ኢንጂነር ነስሪዲን ሐሰን ሃሳባቸውንና አረዓያ ሰብነታቸውን በስፋት ይቃኛል ፡፡
በህይወት ውስጥ አምሳለ አኗኗር ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ታሪክና ሃሳባቸውን አጉልቶ ማሳየት ፤ ለትውልድ የስኬት ጉዞ ቀና ጎዳናን መተለም ነው ያሉት በመጽሃፉ ምረቃ ላይ የታደሙት የድሬዳዋ አስተዳር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም የሱፍ ናቸው፡፡
በሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ እንደዚሁም ኤለሞ ዓሊ ፣ ፈልመታ ሮሮ ፣ አርቲስት ኢብሮሼ እና ድምጻዊ አዴሮ ሙክታርን ጨምሮ ለኦሮሞ ኪነጥበብ እድገት ተቆርቋሪው አቶ ያደታ ጁኔዲ በርካታ የስነጽሁፍ አፍቃሪያን የድሬዳዋ ከተማ ወጣቶች በመታደም የ “ሒጋ“ መጽሃፍ ምረቃ ስነስርዓቱን አድምቀውታል ፡፡
የ” ሒጋ “ መጽሃፍ ደራሲ ወጣት ነስረዲን ሐሰን በሲቪል ኢንጂነሪንግ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀ ሲሆን ያለውን የስነጽሁፍ ተሰጥኦ “ ነስሩ ኩሽ “ በሚል ስም በማህበራዊ ሚዲያ ለተደራሲያኑ ሲያካፍል መቆየቱ በምጽሃፉ ምረቃ መድረክ ላይ ተገልጿል ፡፡
ከኪነ ጥበብና ከከያኒያን ጎን በመቆም ድጋፍ በማድረግ የሚታወቁት አቶ ያደታ ጁኔዲ ወጣቱን ደራሲ ለማበረታታት መጽሃፉን በአንድ ሚሊየን ብር ገዝተዋል ፡፡
ደራሲው ወጣት ኢንጂነር ነስረዲን ሐሰን መጽሐፉ ታትሞ ለአንባቢያን እንዲደርስ ከጅማሮው አንስቶ አብረውት ለነበሩ ሁሉ ምስጋናውን አቅርቦ ፣ በተለይም የመጽሃፉ ምረቃ በደመቀ ሁኔታ እንዲከናወን አስተዋጾ ላደረጉ አካላት ያለውን አክብሮት ገልጿል፡፡


