በዚህም የእግር ኳስ ጨዋታ መርሀ ግብር የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጅሀርን ጨምሮ የካቢኔ አባላት እና የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የሚያካሂዱት የእግር ኳስ ጨዋታ ተጀምሯል ።
የድሬዳዋ አስተዳደር የእግር ኳስ ጨዋታ ስቴዲየም የፊፋ እና ካፍ መስፈርቶችን የሚያሟላ አለም አቀፍ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችለውን ደረጃ በማሟላት በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ከ ኡጋንዳ አቻው ጋር የሚያደርገውን የወዳጅነት ጨዋታውን ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ ነው።


