በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልች ከድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግሥት ሀላፊዎች ጋር በትብብር ሊሰሩ በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል ።
አምባሳደሩ እንግሊዝ ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር ከዚህ በፊት በጀመረቻቸው እና በአዳዲስ የልማት እቅዶች ላይ በትብብር ለመሥራት ፍላጎት ያላት መሆኑን ተናግረዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ከዚህ በፊት በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በትምህርት ና ስልጠና፣ በኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ከአስተዳደሩ ጋር በትብብር እየሰሩ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩም ጠይቀዋል።
በኢንቨስትመንት አማራጮች ላይም የሀገራቱን ባለሀብቶችን ለመሳብ እና በቅርስ እና ጥበቃ ዙሪያ በትብብር ለመሥራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል ።
በተመሳሳይ ዜና አምባሳደሩ በድሬዳዋ አስተዳደር በእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ የሚደረጉ ፕሮጀክቶችን የጎበኙ ሲሆን በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት (one wash),በጤና፣ በሴፍትኔት፣ በቅርስ ጥበቃ እና እንክብካቤ የተሰሩ ተግባራት እንዳስደሰታቸው ገልጸው በተለይም በመጠጥ ውሃ አቅርቦት የለገ-ኦዳ ፕሮጀክትን በመጎብፕት ከዚህ በፊት የነበረውን ድጋፍ በእጥፍ ለማሳደግ እና በይበልጥም በአዳዲስ የልማት እቅዶች ላይ ለመስራትም ቃል ገብተዋል ።


