በህዝብ ቅሬታ እና አቤቱታ አፈታት ላይ ያተኮረ ስልጠና በድሬደዋ ለሚገኙ ሁሉም የወረዳ እና ገጠር ክላስተር አመራሮች እና ባለሙያወዎች እንዲሁም ከሚመለከታቸው ሴክተር ተቋማትን ለተውጣጡ ለለውጥና መልካም አስተዳደር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እና ለሰው ሀብት አመራሮች ስልጠና ተሰጠ ተሰጠ።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት በከተማም ሆነ በገጠር በመንግስት የአገልጋይነት ቦታ ላይ ተቀምጠው ህዝብን እንዲያገለግሉ እድሉን ያገኙ አመራርም ሆነ ባለሙያዎች የህዝብን ፍላጎት ተረድተው ባግባቡ የሚፈልገውን አገልግሎት እንዲያገኝ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በተለይ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚያገለግሉ የወረዳ እና የገጠር ክላስተር አመራሮች ለአገልግሎት አሰጣጥ ተግዳሮት የሆኑ ቢሮክራሲዎችን እና ለመልካም አስተዳደር መንስኤ የሆኑ ችግሮችን አጥርተው በመለየት ለተሻለ ግልጋሎት እንዲሰሩ አሳስበዋል። በስልጠናው በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በተሻሻለው የመልካም አስተዳደር መርሆች ትግበራ ላይ በሚቀርቡ ሰነዶች ላይ በመወያየት ግብአት ሊሆኑ ሚችሉ ሀሳቦች እንደሚቀርቡ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
ቅሬታዎች በጊዜ ካልተፈቱ አቤቱታውም ምላሽ ካላገኘ የህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግር ስለሚሆኑ ሁሉም አመራርም ሆነ ባለሙያ ይህን በመረዳት ለችግሩ መፍትሄ ሚሆኑ አሰራሮችን መዘርጋት ላይ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።
የእለቱ ስልጠናም አገልጋዩ ተገልጋይ አቤቱታ እና ቅሬታን ይዞ ሲቀርብ እንዴት ባጭር ጊዜ መፍታት እንደሚችል እና ህጉ በዚህ ረገድ ምን ይላል ሚለውን መነሻ ተደርጎ መሰጠቱን ነው የገለፁት። መድረኩ በድሬደዋ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላትን እንደገና ለማቋቋም ተግባርና ኃላፊነታቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 68/2014 ላይ ግንዛቤ ሚፈጥሩ ፅሁፎችና እንዴት በቀጣይ ተቀናጅቶ በመስራት የህዝብን እርካታ በመፍጠር ለህዝብ ቅሬታ መንስኤ የሆኑ ችግሮችን መፍታት ይቻላል በሚሉት ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩ ከከተማ ወረዳዎች እና ገጠር ክላስተር እንዲሁም ሚመለከታቸው ሴክተር ተቋማት አመራር እና ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።ሲል የከንቲባ ጽ/ቤት የደረሰን መረጃ ያመላክታል


