የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችን ጨምሮ 20 ሚሊየን ወጣቶችን በስልጠና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ስምምነት ተፈረመ

በቀጣዮቹ ስምንት ዓመታት 20 ሚሊየን ወጣቶችን ለማሰልጠን እና 10 ሺህ ወጣቶችን በአሰልጣኞች ስልጠና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ የለውጥ ትውልድ የተሰኘ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ስምምነቱ የተፈረመው በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ብሬክ ስሩ ትሬዲንግ አ.ማ ድርጅት መካከል ነው፡፡

ተከታታይነት ያላቸው የስብዕና ልማት፣ የአስተሳሰብ ለውጥ የልቦና ውቅርን የሚያስተካክሉ ስልጠናዎች መስጠትን ያለመ ነው።

ስልጠናውም በቀጣዮቹ ስምንት ዓመታት በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አሥተዳደሮች እንደሚተገበር የታወቀ ሲሆን በዚህም 20 ሚሊየን ወጣቶችና 10 ሺህ ወጣቶች በአሰልጣኞች ስልጠና ተደራሽ ይሆናሉ መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *