ጤንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለውን ጠቀሜታ በማህበረሰቡ ዘንድ ማሳደግ እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍራኦል ቡልቻ ገለጹ፡፡

የአንድ ሰዓት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሚሊየኖች በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ከተማ አቀፍ የማህበረሰብ ስፖርት ንቅናቄ ተካሒዷል፡፡

የአንድ ሰዓት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሚሊየኖች በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ከተማ አቀፍ የማህበረሰብ ስፖርት በሀገራቀፍ ደረጃ በሶስት ዙሮች ከአስር ሚሊየን ፣ እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር ደግሞ ከመቶ ሺህ ህዝብ በላይ መማሳተፍ መቻሉን ነው የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍራኦል ቡልቻ የገለጹት፡፡

በተለይም ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ዘውትራዊ ልምዱ ማድረግ የሚችልበትን የጠባይ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ግንዛቤን ከፍ ማድረግ ከተቻለ የተሟላ ጤንነት ያለው ዜጋን መፍጠር ያስችላል ብለዋል ኮሚሽነር ፍራኦል ፤

በማህበረሰብ የስፖርት እንቅስቃሴው ላይ ያገኘናቸው ሌተናል ኮረኔል ደረጀ ቡሽራ የሶስተኛ አየር ምድብ አዛዥ ስፖርት ለሰራዊቱ የእለት ተእለት እንቅስቃሴው አካል መሆኑን ገልጸው ፤ እንዲህ ያለው መድረክ ደግሞ ሰራዊቱ ከህብረተሰቡ ጋር ያለውን አብሮነት ለመግለጽ የምንጠቀምበት ነው ብለዋል፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አትሌት ሰለሞን ከበደ ስፖርት በየትኛውም የእድሜ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ አስፈላጊ መሆኑን ገልጾ እንዲህ በጋራ የአካል እንቅስቃሴ የሚከናወንባቸው መድረኮች መበራከት ቢችሉ የማህበረሰብ ጠባይ ለውጥ ማምጣት የሚቻልበትን እድል ያሳድጋል ይላል ፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በማዘወተር ከሰውነት ክብደት መጨመር እና ከእድሜ ጋር ተያይዘው ሊመጡ ከሚችሉ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ራስን መከላከል የቻላል ፤ ይህንንም ዘውትራዊ ልምምዳችን እንዲሆን በማድረግ ጤንነቱ የተሟላ እና ምርታማ ማህበረሰብ እንዲፈጠር የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል ብለዋል የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍራኦል ቡልቻ ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *