የኢፌዴሪ አየር ሀይል የምስራቅ አየር ሀይል ምድብ 128ኛውን የአድዋ ድል በዓል “አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ አመራሮች፣ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በተገኙበት በደማቅ ስነ ስርዓት በፓናል ውይይት ተከብሯል።
በዓሉ ሃገራዊ አንድነትን በፅኑ መሰረት ከሚገነቡ እሴቶች አንዱ ሆኖ እንዲቀጥልና ሰራዊቱ ይህን እሴት አስቀጥሎ ለማስኬድ በሚያስችል መልኩ የአድዋ የድል በዓል እየተከበረ መሆኑ ነው ከመድረኩ የተገለጸው።
በውይይቱም በአድዋ ድል የወረስናቸው እሴቶች በየዘመኑ የገጠሙንን ፈተናዎችን በድል እየተሸገርን ህልውናችንን በማስቀጠል ሀገርና በማፅናት ዘመን ተሸጋሪ ድሎችን እንድንጎናፀፍ ያደረጉን ወርቃማ ሃብቶቻችን በማስቀጠል እና በማጎልበት ታሪክን መድገም ይገባል ሲሉ ገልጸዋል ፡፡


