አንጋፋውን የድሬዳዋ ስታዲየም፥ የፊፋን ደረጃ ያሟላ የሰው ሰራሽ ሣር ሜዳ ባለቤት በማድረግ ሂደት ውስጥ፥ አስተዋፅኦ የነበራችሁ ግለሰብ እና ተቋማት በሙሉ ክብር ይገባችኋል።
ከሁሉም በላይ ግን… ይህ ስኬት እውን እንዲሆን የተሰጠውን ትልቅ ሀላፊነት በብቃት ለተወጣው፥ ለምወደው ወንድሜ ፉአድ ኢብራሂም ያለኝ ልባዊ ምስጋና ከቃላት በላይ ስለሆነ፥ የአስተዳደራችን ነዋሪዎች እንድትመርቁት በክብር እጠይቃለሁ። አለም አቀፉ ስታዲየማችንን ለድሬዎች ሀብት፥ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ ኩራት የማድረግ ጉዟችን ይቀጥላል። በርቱ እንበረታለን!


