ክርስቶስ የደቀመዝሙራቱን እግር ዝቅ ብሎ ያጠበበትን የትህትና ምሳሌ የጸሎተ ሐሙስ ( ህጽበተ ሐሙስ) ስነ-ስርዓት የድሬዳዋ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ብርሃናት ቀለመወርቅ ቢምረው የካህናቱንና የምእመናኑን እግር በማጠብ ፈጽመዋል ፡፡
የድሬዳዋ ወረዳ ሶስት የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞችና እህቶች የጸሎት ስነ-ስርዓቱን ፈጽመው ለሚወጡ ምእመናን ውሃ ዳቦና ንፍሮ አዘጋጀተው በመጠበቅ ያላቸውን ፍቅርና አብሮነት አሳይተዋል ፡፡
ከዚህ ቀደም በተለያዩ መደበኛና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያየሁትን ድሬዳዋ አንዱ የሌላኛውን ሐይማኖት አክብሮ እና ተፋቅሮ የሚኖርባት ብቻ ሳትሆን አብሮነቱንና ፍቅሩን በአደባባይ የሚያሳይበትን ልዩ ውበቷን ለፊልም ቀረጻ በመጣሁበት አጋጣሚ በአካል በማየቴ ልዩ ደስታ ተሰምቶኛል ሲል ከህዝበ ክርስቲያኑ መሃል ለስራ ድሬዳዋ በመጣበት በአጋጣሚ ያገኘነው አርቲስት ዮናስ ሰሎሞን ገልጾልናል ፡፡


