የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት አመራሮችና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

በዛሬው እለት በቢፍቱ ሞል በተዘጋጀው መንግስታዊ ካልሆኑ የትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ሰፊው የትምህርት ተቋማት እና አመራሮች ተገኝተውበታል።

በዚህ መድረክ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ እዚህ የተገኘነው በጋራ ምክክር አድርገን የትምህርት ዘርፉ የተሻለ ጥራት ያለው ስራ ለመስራት ነው ብለዋል።

ባለፉት ወራት በትምህርት ዘርፍ በተደረጉ የዳሰሳ ጥናት ላይ ግምገማዎች፣ የድጋፍና የክትትል ስራዎች ላይ መሰረት በማድረግ የትምህርት ቤት አመራሮችን በሚመለከት የዳሰሳ ጥናት መደረጋቸውን አቶ ሱልጣን አብራርተዋል።

መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የትምህርት ዘርፋን ከመደገፍ አንፃር ምን አይነት ዝግጅት እያደረገ ነው ያለው? ፣ ተቋሙ ላይ ምን እየሰራ ነው የሚገኘው? ፣ እየሰሩበት ያሉ አቅጣጫዎች ነገ ላይ እንደ ሀገር የተያዘውን የትምህርት ፖሊሲ ከማስፈፀም ጋር ተያይዞ ያሉ ከፍተቶች ምንድን ናቸው በሚሉት ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት ላይ የትምህርት ጥራት ከሚቀንሱ ተግባራት ውስጥ የመምህራንና የትምህርት አመራሮች የትምህርት ዝግጅት ማንስ እንደሆነ ከመድረኩ ተገልጿል።

በዚህም እንደማሳያ ከተነሱት ውስጥ አብዛኞቹ የትምህርት ቤት አመራሮች በትምህርት ደረጃቸውና በሞያው የተመረቁ አለመሆን፤ እንዲሁም አመራሮቹና መምህራኑ በመምህርነት ሙያ የሰለጠኑ አለመሆንና ጥቂቶቹ በሙያው ቢመረቁም አፕላይድ መሆናቸው ተጠቅሷል።

አብዛኞቹ የ2 ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የራሳቸው የሆኑ በቂ መምህራን የሌላቸው በትርፍ ጊዜ የሚያስተምሩ/ ፓርታይመሮች መሆናቸው ጨምሮ ተገልጿል::

በመጨረሻም በግል ትምህርት ቤቶች የ2016 ዓ.ም አፈፃፀምን በሰነድ ያቀረቡት የተቋሙ የእቅድ ዝግጅት ከፍተኛ ባለሙያ በወ/ሮ ጌጥበዛ ተስፋዬ የቀረብ ሲሆን በሰነዱ ላይም መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት አመራሮችና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ጥልቅ ውይይት ተደርጓል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *