የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቧቸው ጥያቄዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ቢሰጥባቸው ያሏቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶችን እያቀረቡ ይገኛል፡፡

ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከልም፡-

• የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጻም በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና፤ ለስምምነቱ መፈፀም መንግስት ከባለድርሻ አካለት ጋር እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች?

• በኮሪደር ልማቱ በታቀፉ አካባቢዎች በዝቅተኛ የንግድ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ዜጎች ለከፋ ችግር እንዳይዳረጉ እና በተሻለ ሁኔታ ለማቋቋም ምን እየተሰራ ነው፤ የኮሪደር ልማቱ ወደ ሌሎች ክልሎች እንዲስፋፋስ ምን ታቅዷል?

• የኢትዮጵያ አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ በዋና ዋና አመላካቾች ምን ደረጃ ላይ ነው ?

• የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ንረትን ከመቀነስ አንጻር እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለማሻሻል መንግስት ምን አቅዶ እየሰራ ነው?

• በሀገሪቱ በአርብቶ አደሮችና አርሶ አደሮች አከባቢዎች እተከሰቱ ያሉ የተለያዩ ወረርሽኞችንና በሽታዎችን ለመቀነስ ምን እየተከናወነ ነው?

• ማንኛውም የመንግስት አገልግሎት የሚገኘው በእጅ መንሻ ሆኗል፤ ታዲያ መንስግት ይህን ለመፍታት ምን እየሰራ ነው? በጥቅሉ የመንግስታዊ ሌብነት እና የሙስና ችግሮችን ለመፍታት ምን ታቅዷል?

• በቅርቡ ከቀረበው የኦዲት ሪፖርት ጋር ተያያዞ ብዙ ተቋማት የሃብት ብክነት እየታየባቸው ነው፤ መንግስት ይህን ከመፍታት አንጻር ምን እየሰራ ነው?

• የአዋሽ ኮምቦልቻ ሀራ ገበያ የባቡር መንገድ ከመልሶ ግንባታ አኳያ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

• በትግራይ፣ በአፋር እና በአማራ ክልሎች የመልሶ ማቋቋም ስራዎች በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ የሚሉና ሌሎች ማብራሪያና ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ያሏቸውን ጥያቄዎች የምክር ቤቱ አባላት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *