የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በድሬዳዋ አስተዳደር በዛሬው እለት አጀንዳ ማሰባሰብ የመጀመሪያ ምዕራፍ አስጀመረ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዚህ ቀደም በከተማው ከሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፋ ተወካዮች አስመርጦ ማዘጋጀቱም ይታወቃል ። በዚሁም የምክክር እና የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሀመድ ድሪር መመካከርና መግባባት ብቸኛው የሰላም ተስፋና ዋንኛው የፖለቲካ መፍትሄ መሆኑን ተናግረው በአገራዊ ምክክር ውስጥም መደማመጥ ፣ መከባበር እና መተማመን በእጅጉ እንደሚዳብርም ነው አምባሳደር መሀመድ ድሪር በእለቱ የገለፁት።

በዛሬው እለት በከተማ አስተዳደሩ የተጀመረው አጀንዳ የማሰባሰብ መድረክ ላይም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የወከሉ ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በነፃነት ሀሳቦቻቸውን በመግለፅ የኢትዮጵያን መፃኢ እድል ለመወሰን ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑም ተገልፆል ። አጀንዳ ማሰባሰቡም ከዛሬ ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ሲሆን የአስተዳደሩ ነዋሪዎችም የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት በንቃት እንዲሳተፋ መልዕክት ተላልፏል ።

በመክፈቻ መርሀ-ግብር ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ\ሮ ፈቲህያ አደን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ተገኝተዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *