ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ፦
የፕሪቶሪያ ስምምነት መነሻና መድረሻው ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊተቋማትን ማክበር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከሰሞኑ በተሻሻለው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 1332/2016 አንቀጽ 2 (1) መሠረት ለሕወሐት የምዝገባ ምስክር ወረቀት መስጠቱን ገልጧል። መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ ተቋማት በሕግና በተቋማዊ ነጻነት የሚወስኑትን ውሳኔ ይቀበላል፣ ያደንቃል፣ የለውጡ አንዱ ፍሬ ነውና። ሕወሐት ሕጋዊ ሰውነቱን ያጣው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ…


