ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ማብቃት ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ አለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በአስተዳድሩ ለ21ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ተከብሯል።
በመርሀ ግብሩም ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ካሊድ መሀመድ የዘንድሮ አለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ማብቃት ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ ማክበር ያስፈለገበት አብይት ጉዳይ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለዘላቂ ልማት የሀገራችን እና የዓለማችን የወደፊት ሁኔታን በመቅረጽ ፤ወጣቶች ይህን ለውጥ እንዲመሩ በማስቻል ረገድ የሚጫወተው ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በሀገራችን ኢትዮጵያ የወጣቶች የማህበረሰብ ክፍል ሰፊ እንደመሆኑ ወጣቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማብቃት ብቁ ተወዳዳሪ እና ስራ ፈጣሪ ዜጋን በማፍራት ሀገሪቱ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ማሳካት ይገባልም ነው ያሉት።
በመድረኩም የአስተዳደሩ የሳይንስ ና ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሮቶሬት ዳይሬክተር በአቶ አብድለዚዝ ሻፊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጹሁፍ ቀርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
በመርሃ ግብሩም በድሬዳዋ አስተዳደር በወጣቶች ና ስፖርት ኮሚሽን ወጣቶች ና በጎፍቃድ ማስተባበሪያ ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር አቶ ባህር አብደላ፣ የማህበረሰብ አንቂ ዶ/ር ኢብሳ አብድሌ ፣የአስተዳደሩ የወረዳ አመራሮች እና በርካታ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል።


