“ቁልፍ የመሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉአላዊነት” በሚል 5 ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት አንድ ጀምሮ እየተከበረ ሲገኝ ይህንንም አስመልክቶ ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ትግበራ እና የባለድርሻ አካላት ሚና በሚል ርዕስ ከክልልና ከከተማ አስተዳደር አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ነው ወ/ሮ ትዕግስት ወደ ድሬዳዋ የገቡት::
በዚህም ጥቅምት 25 እና 26/2017 አ.ም ውይይት የሚደረግ ሲሆን በነገው እለት በዲጂታል ኢኮኖሚ የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል መታወቂያ ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋረ ውይይት እንደሚደረግ ከወዲሁ ታውቋል::
በወ/ሮ ትግስት አምዴ የተመራው ልኡካን ቡድን ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህና በሌሎችም የመስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል::
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ቴድሮስ ልኡልሰገድ


