ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን መከላከል የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ

#DGC ጥቅምት 28/2017

የድሬዳዋ አስተዳደር የስነ-ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ከተለያዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች ሙስና ወንጀሎችን መከላከል ፤ በስነ-ምግባራዊ አመራር እና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ።

የድሬዳዋ አስተዳደር የስነ-ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ፌኑስ አብዱጀባር በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ሙስና የአንድን ሀገር ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገትን በመግታት ረገድ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ገልጸዋል፡፡

እንደ ሀገር ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ስትራቴጂ ተነድፎ ተግባራዊ መደረጉን ያነሱት ኃላፊው እንደ አስተዳደርም የተቀናጀ ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥ የሚሆን የሠራተኞች ንቅናቄ በመፍጠር የትግሉ አካል በማድረግ፣ በሥነ-ምግባር ግንባታ፣ ሙስናና ብልሹ አሠራሮችን በመከላከል ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ትኩረት ተሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

በመሆኑም ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ዘመቻ የሚታዩትን ክፍተቶች ለመሙላት እና የስነ ምግባር ግንባታውን በማጠናከር ስራውን ለማሻገር በየደረጃው የሚገኘውን ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉም ነው የአስተዳደሩ የስነ-ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ፌኑስ ያሳሰቡት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *