በ 2017 በጀት አመት ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገለፀ

#DGC ህዳር 23/2016

በድሬዳዋ አስተዳደር በ 2017 በጀት አመት የመጀመሪያ 4 ወራት የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ አፈፃፀምን አስመልክቶ የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት የመሰረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኢብሳ አሜ በዛሬው እለት ለሚዲያ አባላት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል ።

ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ አሰባሰብ ጋር ተያይዞ በያዝነው አመት ውጤታማ የሆኑ ስራዎች እንደተሰሩና ለዚህም ማሳያ የሚሆነው የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ካለፈው አመት አንፃር የ 20 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለውና ይህም ሊሆን የቻለው በቅንጅት በመሰራቱ መሆኑን አቶ ኢብሳ አሜ ተናግረዋል ።

በያዝነው አመት ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ለመሰብሰብ የታቀደው እቅድ ለመጀሪያ ጊዜ ከመሆኑም በላይ እቅዱ እንዲሳካም የጋራ እቅድ ከማውጣት አንስቶ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩና እቅዱንም ለማሳካት ይቻል ዘንድም የፋይናንስ ድጋፍ ከመደረጉም በላይ የተለያዩ ጥናቶች ተጠንተው ወደ ስራ ያልገቡ ኮዶች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉንም ነው አቶ ኢብሳ ያስታወቁት ።

በድሬዳዋ ላይ ያሉ የእንግዳ ማረፊያ ያላቸው ማንኛውም ሆቴሎች እና ፔንሲዮኖች ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ የመሰብሰብ ሂደት እንደሚጀመር አቶ ኢብሳ ተናግረው ከዚህ በተጨምሪም በቄራ በኩል ስጋዎችን አሳርደው ለገበያ የሚያቀርቡ ሆቴል ቤቶች እንዳሉ ሁሉ በህገ-ወጥ መንገድም አሳርደው ለገበያ የሚያቀርቡ ሆቴል ቤቶች እንዳሉና ከዚህ በኃላ ግን የእርድ ከብቱን በማስመርመርና አስፈላጊውን ክፍያ በመክፈል ለገበያ ማቅረብ የሚችሉበትን መንገድ መፈጠሩንም ነው አቶ ኢብሳ ያስታወቁት ።

ከጫኝ እና አውራጅ ጋር ተያይዞ በአስተዳደሩ ላይ በርካታ ጫኝ እና አውራጅ ማህበራት ያሉ ሲሆን እነዚህም ማህበራት በተቀመጠው ታሪፍ መሰረት የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን መክፈል እንደሚገባቸው ገልፀው ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ግንባታዎች ሲካሄዱ በአካባቢው ላይ የሚኖረውን ተረፈ ምርቶች እዛው በመተዋቸው ምክንያት ከፍተኛ ችግሮችን ሲፈጥር እንደቆየና ከዚህ በኋላ ማንኛውም ህንፃ የሚያሰሩ በግንባታ ወቅት ለሚያስቀምጡት ተረፈ ምርቶች በካሬ መክፈል እንደሚገባቸውም ነው አቶ ኡብሳ አሜ በዛሬው እለት ለሚዲያ አባላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ያስታወቁት ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ :- ሰላም አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *