ልባችንን ወደ ሰላም በመመለስ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ በጋራ እንስራ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ልባችንን ወደ ሰላም እና ወደ ፍቅር በመመለስ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ በጋራ እንስራ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ተቀድታ የማታልቅ ባህር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ሀገሪቱን በየቀኑ ለመቅረብ መሞከር የተሻለ ዕውቀት ለመሰነቅ እንደሚያግዝ አስገንዝበዋል፡፡

ሀገሪቱ ተዝቆ የማያልቅ ሐብት ባለቤት መሆኗን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፤ በቁንጽል ዕውቀት ኢትዮጵያን ለማብራራት ከመሞከር ይልቅ በአቃፊነት እሳቤ አብሮነትን ማጎልበት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው አንድነት እና ዕድገት በመደመር እሳቤ እና በህብረ ብሄረዊነት ትርክት በጋራ መቆም እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያን አውቀን አልጨረስናትም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ የጋራ ታሪክ፣ የጋራ ባህል፣ የጋራ ውርስ እና የጋራ መስዕዋትነት መኖሩንም ገልጸዋል፡፡

19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *