ዜና እረፍት

ከድሬዳዋ አስተዳደር የተላለፈ የሀዘን መግለጫ

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ስር በሚገኘው በድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል እንዲሁም በግል ጤና ተቋማቸው ሮቃ ክሊኒክ ለድሬዳዋና ህብረተሰብና ለአካባቢው አጎራባች ክልሎች የህክምና አገልግሎት ከመስጠት ባለፈም የህዝብ ተጠሪ በመሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አባል በመሆን ሲያገለግል የቆዩትና የኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ ህሙማንን በሙያቸው በመደገፍና በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎት ላይ በመሳተፍ የሚታወቀው ዶ/ር አቤል መልካሙ በደረሰባቸው ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የድሬዳዋ አስተዳደር የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ፈጣሪ መፅናናቱን ይሰጥ ዘንድ በአስተዳደሩ ስም እንመኛለን ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *