#DGC ታህሳስ 1/2017
በድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የከተማ ምግብ ዋስትና ዳይሬክቶሬት በዛሬው እለት የ2017 ዓ.ም በአዲስ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ስራ ፕሮጀክት ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎችን አጠቃላይ ተግባራቶች ለስትሪንግ ኮሚቴው ያቀረበ ሲሆን ስትሪንግ ኮሚቴውም በቀረበው ሰነድ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።
በዚህም በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በድሬዳዋ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ስራ ፕሮጀክት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ ዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ገልፀው፤ ስራዎችን በቅንጅት በመስራት በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ማጠናቅቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ምክትል ከንቲባ ሀርቢ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች በቀጣይ ወደ አካባቢ ልማትና ቀጥታ ድጋፍ እንዲገቡ ለማድረግ የተጠቃሚዎች ልየታ በጥንቃቄ ማካሄድ እንደሚገባ አመላክተዋል።
የከተማ ምግብ ዋስትና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መይደኔ በበኩላቸው በፕሮጀክቱ አዲስ ተጠቃሚዎችን ልየታ ለማካሄድ ከስትሪንግ ኮሚቴው ጋር ውይይት መደረጉን ገልፀው፤ ዘንድሮ እንደ ድሬዳዋ 1.29 ፐርሰንት ማለትም በአጠቃላይ 9035 ዜጎች በዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:- የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት


