በዚህም በውይይቱ በቀጣይ ፓኪስታንና ድሬዳዋ በተለያዩ ዘርፎች አብሮ ለመስራት በመድረኩ የተነጋገሩ ሲሆን፤ በተለይም የአምራች ኢንደስትሪውን ዘርፍ በማሳደግና የፓኪስታን ኢንቬስተሮችን ወደ ድሬዳዋ በመሳብ በተለያዩ ዘርፎች እንዲሰማሩ ለማድረግ በትብብርና በቅንጅት እንደሚሰራ ከመድረኩ ተገልጿል።
ከውይይቱ በመቀጠልም አንባሳደሩ የድሬዳዋን ነፃ የንግድ ቀጠና እንዲሁም ደረቅ ወደብን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን፤ ድሬዳዋ በኢንደስትሪው ዘርፍ የሚበረታታ ስራዎችን እየሰራች እንደምትገኝ መመልከታቸውን አንባሳደር አጢፍ ተናግረዋል።
አንባሳደሩ አያይዘውም በቀጣም ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር በመቀራረብና ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ በጋራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በኤደን ሳሙኤል


