ልባችንን ወደ ሰላም በመመለስ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ በጋራ እንስራ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ልባችንን ወደ ሰላም እና ወደ ፍቅር በመመለስ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ በጋራ እንስራ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ተቀድታ የማታልቅ ባህር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ሀገሪቱን በየቀኑ ለመቅረብ መሞከር የተሻለ ዕውቀት ለመሰነቅ እንደሚያግዝ አስገንዝበዋል፡፡ ሀገሪቱ ተዝቆ የማያልቅ ሐብት ባለቤት መሆኗን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፤ በቁንጽል ዕውቀት ኢትዮጵያን ለማብራራት ከመሞከር ይልቅ…


