አሽከርካሪዎች መሰል መድረኮች ሊጠናከሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ሶስተኛ ቀኑን በያዘውና በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎችን በተሻሻለው የመንገድ ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 ላይ የግንዛቤ ለማስጨበጫ የተዘጋጀው መድረክ ማጠናቀቂያውን አድርጓል።
በመድረኩ የደንቡ መሻሻል ባስፈለገባቸው ነጥቦችና በደንቡ የተካተቱ የጥፋት እርከኖች ላይ ለመንግስት ተሽከርካሪ ሹፌሮች ማብራሪያ ሰቷል።
የቀረበውን ሰነድ መነሻ በማድረግም አሽከርካሪዎች ባነሱት ሀሳብ ተሽከርካሪዎቻችን በወቅቱ ሰርቪስ አይደረጉም ብልሽት ሲገጥማቸው ወቅታዊ ጥገና ባለማግኘታቸው እንዲሁም አስፈላጊውን ሰነድ ባለሟሟላት በህግ መተላለፍ ለቅጣት እየተዳረግን ነውና በነኝህ ነጥቦች ላይ ለተቋም ሀላፊዎች ግንዛቤ ቢፈጠር ብለዋል።
ሌላው የአንዳንድ ታክሲ ሹፌሮች የመንገድ አጠቃቀም ላደጋ ይጋብዛልና ቢታረም ብለዋል።
የወጣው ደንብ ማስተማርን እያስቀደመ ቢተገበር መሻሻሎችን ይፈጥራል ብለዋል።
በተረፈ ከረጅም አመት በኋላ ትኩረት ሰታችሁ ስለሰበሰባችሁን እናመሰግናለን ይህ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያም የባለስልጣኑ የመንገድ ደህንነት እና መድህን ፈንድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጅነር ሁሴን ጀማል እኛ ራሱንም ሆነ ማህበረሰቡን ከአደጋ ጠብቆ በጥንቃቄ ሚያሽከረክር አሽከርካሪን መፍጠር እንጂ ቅጣት አደለም አላማችን ያሉ ሲሆን ተመክሮ ያልሰማውን ስርአት ለማስያዝ ግን ህጉ ይሄን ይመስላል ሚለውን ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ መድረክ ነው ብለዋል።
በአሽከርካሪው የተነሱ ሀሳቦችን ይዘናል ከሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች በመምከር እና በተቋማችን ለሁሉም ተቋማት ተሽከርካሪዎችየቴክኒክ ምርመራ በማድረግ ለተነሱት መፍትሄ ለመስጠት እንጥራለን ብለዋል።እናንተ ግን በህግና ባግባብ በማሽከርከር አርአያ ልትሆኑ ይገባል ነው ያሉት።


