የድሬዳዋ አስተዳደር ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ “ሀይማኖቶች ለሰላምና ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም በድሬዳዋ አስተዳደር የሚካሄደውን የሰላም ኮንፍረንስን አስመልክቶ ለፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ኦረንቴሽን ሰጠ

በዚህም በመድረኩ ከሰባቱም የእምነት ተቋማት የተውጣጡ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።

በኦረንቴሽኑ ወቅት ያነጋገርናቸው ወጣቶችም የሀይማኖት ተቋማት ስለ አንድነት፣ ስለ ሰላም እና ህብረት ሁሌም እያስተማሩ እንደሚገኙ አንስተው፤ እኛ ወጣቶችም የድሬዳዋን ሰላምና አብሮነት እንደ ሁሌውም አጠናክረን የማስቀጠል ሀላፊነት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

ድሬዳዋ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰላም ኮንፍረንስ ሊዘጋጅባት መሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ተሳታፊዎቹ አያይዘው ገልፀዋል።

በመጨረሻም ወጣቶቹ ኮንፍረንሱ ላይ ለመታደም የሚመጡ እንግዶችን በተለመደው የድሬዳዋ ፍቅር ተቀብለን ለማስተናገድ ዝግጁ ነን ሲሉ አመላክተዋል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-ሰላም አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *