“ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል ” በሚል መሪ ሀሳብ በዓለም ለ 21 ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ 20 ኛ ጊዜ የአለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ መርሀ-ግብሮች የሚከበር ሲሆን ይህንንም አስመልክቶ በዛሬው እለት የተማሪዎች የአሸናፊዎች አሸናፊ ጥያቄና መልስ ውድድር አካሂደዋል ።
ሙስና በተለይም የራስ ያልሆነን ነገር በአቋራጭ እና በጉልበት በማጭበርበር የራስ ማድረግን ጨምሮ ለሀገራት እድገት ማነቆ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፌኑስ አብዱልጀባር ተናግረው መምህራን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤቶች ላይ ያሉ ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የራሳቸውን ከፍተኛ አስተዋፆ መወጣት እንዳለባቸው ሁሉ ተማሪዎችም በስነ-ምግባር የታነፁ ከመሆናቸውም በላይ በትምህርታቸውም ውጤታማ የሆኑ ተማሪዎች ሊሆኑ እንደሚገባም ነው የተናገሩት ።
አቶ ፌኑስ አክለውም ሙስናን የመከላከል እና የመቆጣጠሩ ስራ የሁሉም ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረው በተለይም ወላጆች ፣ መምህራን እንዲሁም ተማሪዎች በቀጣይ ስለ ሙስና ማስተማር ፣ ማወያየት እና ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸውም ነው ያስታወቁት ።
በቀጣይም አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ በተለያዩ መርሀ-ግብሮች የሚከበርም ይሆናል።
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- በሰላም አበበ


