በዘላቂ የልማት ግብ ላይ ትኩረት ያደረገ የወጣቶች የንቅናቄ መድረክ በድሬዳዋ ሊካሄድ ነዉ::

ወጣቶችን በዘላቂ ሰላም እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ተሳትፎቸውን ለማሳደግ እና ለማጠናከር የሚያስችል የድሬ ወጣቶች ፎረም መድረክ ሊካሄድ መሆኑን የድሬዳዋ ወጣቶች ምክር ቤት፣የስካውት ካውንስል እና የከፍታ ወጣቶች ጥምረት ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶች በዘላቂ የልማት ግቦች ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር አለም አቀፍ እሳቤ እንዲኖራቸው ከማስቻል ባለፈ የመፍትሄ አካል በመሆን በሀገር እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተሳትፏቸው ለማሳደግ እና ተጠቃሚነታቸውን ለመፍጠር የሚያስችል ድሬ ፎረም የተሰኝ አስተዳደር አቀፍ የወጣቶች ፎረም ከታህሳስ 25 _26 ደረስ ሰፊ የወጣቶች የንቅናቄ መድረክ ሊካሄድ መሆኑን የድሬዳዋ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና የድሬ ፎረም ሰብሳቢ አቶ አሚድ አብደላ አስታውቀዋል ።

“ወጣቶች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ለአየር ንብረት ለውጥ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው የወጣቶች የንቅናቄ መድረክ ከ300 በላይ የአስተዳደሩ ወጣቶች በቀጥታ የሚሳተፉ ሲሆን ከ200 በላይ ወጣቶች በበይነ መረብ የሚከታተሉት መሆኑም ተገልጿል።

የድሬ ወጣቶች ፎረም ለአስተዳደሩ ወጣቶች በአመራር፣ በስራ ፈጠራ፣ በኢኮኖሚ፣ ሰላም በማስፈን ላይ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ እንዲኖራቸው መድረኩ ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል።

በመሆኑም የአስተዳደሩ ወጣቶች በሚካሄደው የድሬ ወጣቶች የንቅናቄ ፎረም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ሲሉ የድሬዳዋ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና የድሬ ፎረም ሰብሳቢ አቶ አሚድ ጥሪ አቅርበዋል።

በሰላም ለማ

ምስል:- ሰላም አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *