ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ይህን ያሉት በትላንትናው እለት ከሰዓት በኋላ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነዉ ።
በውይይቱም በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ እና በሳቸው አመራር ሰጪነት የሚመራው የለውጥ ሀይል የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልጽግና ከማረጋገጥ አንጻር ያስቀመጧቸውን ግቦች በተጨባጭ ተግባራዊ እየሆኑ ና የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያበስሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በቱርክ ሀገር ሲደረግ የነበረው የኢትዮጲያ እና የሶማሊያ ድርድር በስምምነት መጠናቀቁ ለሁለቱም ሀገራት በተለይም ለአፍሪቃ ቀንድ ቀጠናዊ ሰላም ወሳኝ ሚና እንዳለውም ገልፁዋል።
ከንቲባው በመቀጠልም የኢትዮጲያና የሶማሊያ ህዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና በደም የተሳሰርን እንደመሆናቸን መጠን ለጋራ ሰላምና ልማት አብረን ለመስራት ቁርጠኛ የሚያደርገን ነው ብሏል።
በመድረኩም የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በሶማሊያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ ወደብ በምታገኝበት አማራጭ ላይ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር መስማማታቸው በዲፖሎማሲ የተገኙ ስኬቶችን የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር ሁለቱም አገራት ተያይዘው አብረው በማደግና ከድህነት ለመላቀቅ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ትልቅ መሰረት የሚጥል ስለመሆኑን ተናግሯል ፡፡
ሁለቱ ሃገራት የፈረሙት ሰነድ ትብብርን፣ የኢኮኖሚ እድገትን እና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም በድሬዳዋ አስተዳደር የሚሰጡ መንግስታዊ አገልግሎቶችን ጥራት በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶች ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ይህም የአስተዳደሩና የኢትዮጵያን ከፍታ ጅማሮ ያበሰረ መሆኑ ተገልፃል።
በመጨረሻም በተጨባጭ ሁለንተናዉ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ተግባራዊ እየሆኑ ያሉ ፈጣን የልማት ጉዞዎችን በማስቀጠል ረገድ አመራሩ እና አባላቱ ግንባር ቀደም በመሆን የተቀመጠውን ግብ በማሳካት ደርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
በሰላም ለማ
ምስል:- አገኝው ሸዋረጋ


