ከሰሞኑ በኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስትር ክቡር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ የተመራ ልዑክ በድሬዳዋ አስተዳደር እየተሰሩ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን አፈፃፀም ለመገምገም ያለመ ሱፐርቪዥን በማድረግ ላይ ሲሆን በዛሬው እለትም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እና ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች በተገኙበት የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ተጠሪ ተቋማ የሆነው ድሬዳዋ ስራ አመራር ኢንስቲትዩትን የሁለተኛው ምዕራፍ የግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡
ለልዑካን ቡድኑ ማብራሪያ የሰጡት የድሬዳዋ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወቀ ለገሰ እንደገለፁት አጠቃላይ የኢንሴቲትዩቱ የግንባታ ፕሮጀክት በ 3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ መሆኑን ጠቅሰው በመጀመሪያው ምዕራፍም አንድ የG+2 የማስተማሪያ/ማሰልጠኛ ህንፃ፣ አንድ የG+2 የአስተዳደር ህንፃ እና አንድ የG+1 የኤግዚቢሽን ህንፃ የግንባታ ስራን በማጠናቀቅ ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም አስመርቀው ወደ ስራ በማስገባታቸውን ተናግረዋል።
በሁለተኛው ምዕራፍም ሁለት ዘመናዊ የስልጠና አዳራሾች ፣ አንድ ዘመናዊ የካፍቴሪያ አገልግሎት የሚሰጥ ህንፃ ከግዙፍ የመኪና ማቆሚያ ጋር እንዲሁም የአንድ ዘመናዊ ሁለገብ ላይበራሪ ህንፃ ፕሮጀክት ግንባታ በመከናወን ላይ መሆኑን የገለፁት አቶ አወቀ የፕሮጀክቱ አፈፃፀምም 70% መድረሱን ተናግረዋል።
አቶ አወቀ አክለውም የህፃ ግንባታው ኢንስቲትዩቱ በአስተዳደራችን ብሎም በምስራቅ ኢትዮጲያ የስራ አመራር ጥበብ ማፍለቂያ የመሆን ራዕይውን ለማሳክት በሚያስችል አግባብ ለስልጠና፣ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ለምክር አገልግሎት ምቹ ፣ የተሟላ፣ ዘመናዊና ደረጃውን´
በጠበቀ መልኩ በመገንባት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ በ 45ዐ,ዐ00000 ብር ጠቅላላ ወጪ የሚገነባ ሲሆን ፕሮጀክቱ አሁን ያለበት የአፈፃፀም ደረጃ 68% እንደሆነና እስካሁን ለ 590 ዜጎች (ወንድ፤355 ሴት235) የስራ ዕድል መፍጠሩን እንዲሁም ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም ከ 25,000 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች አገልግሎት የመስጠት አቅም እንዳሚኖረውም ነው የተገለፀው።


