ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ዘመናዊ የመልካም አስተዳደር ቅሬታዎች አፈታት አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ::
በድሬዳዋ አስተዳደር የመልካም አስተዳደር እና ቅሬታ አፈታት ዙሪያ የተከናወኑ ስራዎችን ድጋፍና ክትትል ማድረግ አላማ ያደረገ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የተውጣጣ ልዑክ በድሬደዋ ቆይታ አድርጓል። በአስተዳደሩ የተሻለ አፈፃፀም ያሳዩ የሴክተር ተቋማትና ወረዳዎች በመልካም አስተዳደር የችግር አፈታት እና ቅሬታ ዙሪያ ያከናወኑትን ስራዎች ከፌዴራል ለተገኙት አካላት በዝርዝር በማቅረብ ውይይት ተካሂዷል። ልዑኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ከህዝቡ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ምላሽ አሰጣጥ ሂደት…


