የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅን ነገ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል::

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያደርገው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ እንደሚያፀድቀው ይጠበቃል።

በስብሰባው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብ ይሆናል።

ምክር ቤቱም ቋሚ ኮሚቴው የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

ረቂቅ አዋጁ ሰኔ 18 ቀን፣ 2ዐ16 ዓ.ም ለፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መመራቱን የምክር ቤቱ መረጃ አስታውሷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *