በአስተዳደሩ ላይ የሚገኙ የህንፃ ግንባታ ስፍራዎች ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መታጠር እንዳለባቸው ተገለፀ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ባለስልጣን በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን ውስጥ በአስተዳደሩ የንግድ ቤቶች ፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና የንግድ ድርጅቶች ማስታወቂያ ፍቃድ መስጠትና ማደስ ቢልቦርድና መሰል በህንፃዎች ላይ ተለጣፊና ተንጠልጣይ ማስታወቂያዎችን ፍቃድ መስጠት ማደስና አመታዊ እድሳት የሚያደርጉ ማስታወቂያዎችን መቆጣጠር እንደመሆኑ መጠን በአስተዳደሩ ላይ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተተከሉ የማስታወቂያ ሳጥኖች እና ቢልቦርዶች ፍቃድ ከማውጣት አንስቶ ህግ እና ደንቡን ተከትለው መስራት እንደሚገባቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ህንፃ ሹም የሆኑት አቶ ኤፍሬም ግርማይ ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ ግንባታዎች በሚካሄዱበት ጊዜ በግንባታ አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ አጥሮች የከተማውን ውበት በጠበቀ መልኩ ከማድረግ ባለፈ ደረጃውን በጠበቀ ኤጋ ቆርቆሮ በማጠር አጥሩንም ቢጫና አረንጓዴ ቀለሞች መቀባት እንደሚገባም ተናግረዋል ።

የኢትዮጵያ ህንፃ አዋጅ በሚደነግገው መሰረት በአስተዳደሩ የሚገኙ ማንኛውም ደረጃ ” ሐ ” የሆነ ህንፃ ለአገልግሎት ብቁ በሚሆንበት ወቅት ወደ አገልግሎት ከመግባቱ በፊት መጠቀሚያ ፍቃድ ማውጣት እና ፍቃዱንም በየአመቱ ማደስ እንደሚገባ ህንፃ ሹም ኤፍሬም ግርማይ ተናግረው በስራ ቀናትም ወደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመምጣት የህንፃ መጠቀሚያ ፍቃድ ማውጣት እንደሚገባና በተሰጠው ቀነ ገደብ አልሚዎች ከላይ የተጠቀሱትን ፍቃዶች እና የፍቃድ እድሳቶች ማከናወን እንደሚገባቸውም ነው ህንፃ ሹም አቶ ኤፍሬም ግርማይ ተናግረዋል ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ :- ሰላም አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *