ልዑክ ቡድኑ በዛሬው እለት ጠዋት ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስም በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና በመስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
“ሄር ኢሴ” ያልተጻፈ ባህላዊ ህግ ዓለም አቀፍ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ አባላት በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።
ሄር ኢሴ” ባህላዊ መተዳደሪያ ህግ በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን በ16ተኛው ክፍል ዘመን 44 የኢሣ ማህበረሰብ አባላት ተቀምጠው ያጸደቁት ሲሆን የቅርሱ መመዝገብ የተሻለ ጥበቃና እንክብካቤ ለማድረግ የሚያግዝ ነው።
“ሄር ኢሴ” ባህላዊ ህግ በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ ያሉ የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ አባላት በግልጽ አሰራር የሚፈጸም፣ በፍትሐዊነት እና በእኩልነት ማህበረሰቡን የሚያገለግል የፍትህ ስርዓት ነው።
ታዲያ ከዚህ አንጻር የሕጉ በቅርስነት መመዝገብ ለማህበረሰቡ የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:- አገኘሁ ሸዋረጋ


