የኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስትር ክቡር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ የተመራ ልዑክ ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር እየተሰሩ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን አፈፃፀም ተመልክቶ ክትትል እና ድጋፍ
ለማድረግ ያለመ ጉብኝት ሲሆን በዛሬው እለትም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እና ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች በተገኙበት የኡኖ ውሃ ፋብሪካ ፣የማርብል ጉሩፕ ግራናይት ፋብሪካ፣ የብራ ኮፊ ትሬዲንግን እንዲሁም የአስተዳደሩ ገቢዎች ባለስልጣን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በጉብኝቱም አስተዳደሩ በኢንቨስትመንትን ዘርፍ ለአምራች ኢንዱስትሪው የተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑ ለኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ምክኒያት መሆኑ ተጠቅሷል።
በሰላም ለማ
ምስል:- ረመዳን አደም


