የድርጅቱ ፕሬዝዳንት ፓውላ ኤሪክ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሃርቢ ቡህ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ሀላፊ ገበየሁ ጥላሁን፣ ኮሚሽነር አለሙ መግራ እና የአስተዳደሩ አደጋ ስጋት ኮምሽን ኮምሽነር እንዲሁም የዲያስፖራ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፓውላ ኤሪክ በቀጣይ በድሬዳዋ በሚኖራቸው ቆይታ ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን በግብረሰናይ ድርጅታቸው ስም ለተቸገሩ ወገኖች የዘይት እና ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ከድርጅቱ ተወካይ ባለሞያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
dire tv


