የፊደራል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በድሬዳዋ አስተዳደር በመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የድጋፍና ክትትል ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል::

የድጋፍና ክትትል ቡድኑ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደ አስተዳደር በኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የድጋፍና ክትትል ስራ ያከናውናል።

በቢሮ እየተከናወኑ ያሉ ስራዋችን እና በቀጣይ እንደ መንግስት ትኩረት ተሰቶባቸው ሊከናወኑ ይገባል ባሏቸው አንኳር ነጥቦች ላይ ከቢሮው ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ እና ከተቋሙ ማነጅመንት አባላት እንዲሁም ከቡድን መሪዋች ጋር ውይይት አድርገዋል ።

በውይይቱ ማጠቃለያም እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር እየተሰሩ ያሉ የኮሙዩኒኬሽን ስራዋች ጥሩ መሆናቸውን የገለፁት የክትትል እና የድጋፍ ቡድኑ ተቋሙ በሪፎርም ስራው እያከናወናቸው ያለው የዲጅታል አሰራሩ ከጠበቁት በላይ እንደሆነባቸው ገልፀዋል።

የክትትል እና ድጋፍ ቡድኑ ተቋሙ የለውን የስራ እንቅስቃሴም በየክፍሉ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በዛሬ ከሰአት እና በነገው እለት ውሏቸው የሴክተር እና የወረዳ የኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ የስራ እንቅስቃሴ ላይ ድጋፍና ክትትል የሚያደርጉ ይሆናል።

በትዕግስት ቶሎሳ

ፎቶ፦አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *