የኢስተርን ዴቨሎፕመንት ኢኒሺቲቭ (EDI)ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢኒስትቲዩት አለም አቀፍ ድርጅት (LPI)ጋር በመተባበር ባለፉትአመታት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን ድርጅቱ ለወጣቱ የስራ እድል ለመፍጠር በድሬዳዋ አስተዳደር በዘጠኙም ወረዳ አስተዳደሮች ለ 80 ወጣቶችን በስራ ክህሎት እና ኢንተርፕሪንረየርሺፕ ስልጠና ሰቷል፡፡
በስልጠና መድረኩ ማጠቃለያ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢስተርን ዴቨሎፕመንት ኢኒሺየቲቭ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግርማ ቱፋ እንደተናገሩት በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን ለማፋጠን ስራ እና ስራ ፈላጊዎችን ወጣቶችን ማቀራረብ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡
ከዚህም ጋር አያይዘው ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ግርማ በድሬዳዋ አስተዳደር 14 ሺህ የሚደርሱ ስራ ፈላጊዎች ወጣቶች የሚገኙ ሲሆን በተቻለ መጠን ወጣቶችን ከመንግስት ስራ ተቀጣሪነት ስሜት በማውጣት የራሳቸውን ስራ መፍጠር እንዲችሉ የኢስተርን ዴቨሎፕመንት ኢንሺቲቭ (EDI)ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢንስትቲዩት አለም አቀፍ ድርጅት (LPI) ጋር በመተባበር ከድሬዳዋ አስተዳደር በዘጠኙም ወረዳ አስተዳደሮች ለተመለመሉ 80 (ሰማንያ) ስራ ፍላጊ ወጣቶችን በስራ ክህሎት እና ኢንተርፕሪንረየርሺፕ ስልጠና በተሳካ ሁኔታ መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡
የሰለጠኑ ወጣቶች በሚመርጡት የስራ ዘርፍ እንዲሰማሩ ለማስቻል የስራ እድል ፈጠራ ልምድ እና ተሞክሮ እንደዚሁም የፋይናስ ምችችት የሚደረግበትን ምቹ ሁኔታዎች ለመፍጠር የስራ ክህሎት ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮና ባለድርሻ አካላት በስልጠና ማጠናቀቂያ መድረኩ መሳተፋቸውን ጠቁመዋል፡፡
ስራ ፈላጊ ወጣቶችን ቁጥር መቀነስ የመንግስት ብቻ ባለመሆኑ ሁላችንም ጥረት የሚጠይቅ በመሆኑ ሁላችንም የድርሻቸን ለመወጣት መረባረብ ይኖርብናል ሲሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግርማ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመድረኩ የተሳተፉ ባለድርሻ ተቋማትም በቀጣይ ወጣቶች በሚገጥሟቸው እና አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ከጎናቸው እንደሚሆኑ በመግለፅ በሰለጠኑት ሙያ ቁርጠኛ አቋም በመያዝ ወደ ስራ እንዲገቡም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም ስልጠናውን ተከታትለው ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተሰቷል።


