ባለፍት ጊዜያት ወጣቶችን ተጠቃሚና ተሳታፊ የሚያደርጉ በርካታ ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ::

የድሬዳዋ ወጣቶች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ እና የ 2017 ግማሽ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል ። በዚሁ መድረክ ላይም የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ካሊድ መሀመድ በተለይም በበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ ወጣቶች በስፋት እንዲሳተፍ በማድረግ እውቀታቸውን ፣ ጉልበታቸውን እና ክህሎቶቻውን ለማህበረሰብ እድገት እንዲሁም ለሀገር እድገትና ብልፅግና ያበረክቱ ዘንድም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት ።

የድሬዳዋ ወጣቶች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ እና የ 2017 ግማሽ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የሚቀርበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ንቁ ተሳትፎ ከማድረግ ባለፈ 3 ተኛ ሩብ አመት እና 4 ተኛ ሩብ አመትን በተሳካ ሁኔታ እንዲፈፀም የበኩላችሁን አስተዋፆ ማበርከት እንደሚገባቸውም ነው የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን የወጣቶችና በጎ ፍቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ባሃር አብደላ በእለቱ ያስታወቁት ።

የወጣቶች ምክር ቤት በተለይም ወጣቶችን በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ እንዲሳተፍ ከማስቻል ባሻገር የወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ተሳትፎን ከማረጋገጥ አንፃር ዘርፈ-ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የድሬዳዋ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ወጣት ሀሚድ አብደላ ተናግረው ባለፍት ጊዜያትም በሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተሳታፊ መሆን ከመቻሉም በላይ አሁን ላይም ወጣቶችን ተጠቃሚና ተሳታፊ የሚያደርጉ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ነው አቶ ሀሚድ አብደላ የተናገሩት ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ :- ሙሉአለም ደሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *