የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር በክቡር ሙስጠፌ መሀመድ የተመራው ልዑክ ቡድን ድሬዳዋ የገባው በሶማሌ ክልል በሽንሌ ሲቲ ዞን የተጠናቀቁ የልማት ስራዎችን ለማስመረቅ እና ለመጎብኘት መሆኑ ተገልጿል።
ልዑካን ቡድኑ ድሬዳዋ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ፣ምክትል ከንቲባ ናየንግድ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምስል:- አገኝሁ ሸዋረጋ


