የ 2017 በጀት አመት የመጀመሪያ 6 ወራት የመስክ ምልከታና ቁጥጥር ተካሄደ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ 2017 በጀት አመት የመጀመሪያ 6 ወራት ስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ በዛሬው እለት የመስክ ምልከታ እና ቁጥጥር ያካሄደ ሲሆን በጀልዴሳ ክላስተር አያሌ ጉምጉም ቁጥር ሁለት ትምህርት ቤት ፣ ለገዲኒ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ መልካ ቀሮ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም የመልካ ቀሮ ጤና ጣቢያ ላይ የመስክ ምልከታ አድርገዋል ።

በዛሬው እለት በጀልዴሳ ክላስተር በሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች ላይ በነበረው የመስክ ምልከታ ላይም ጥሩ አፈፃፀሞች የታዩ ሲሆን አንዳንድ የታዩ ክፍተቶችንም በቀጣይ በማሻሻል የተሻለ ስራዎችን መስራት እንደሚገባም ነው በእለቱ የተገለፀው ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ :- በሙሉአለም ደሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *