ህብረተሰቡ ግብሩን በአግባቡ እንዲከፍል የሀይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ

    በድሬደዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በተከናወነው የታክስ ንቅናቄ መድረክ ተገኝተው ለንግዱ ማህበረሰብ ግብርን በአግባቡ አለመክፈል በምድርም በሰማይም እንደሚያስጠይቅ ያስተማሩት  የሀይማኖት አባቶች ግብርን በመክፈል ሁሉም ዜጋ ለሀገሪቱ እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡   ከሐምሌ 1 እስከ ሐምሌ 30 የደረጃ 3 (ሐ) ግብር ከፋዮች ግብራቸውን የሚከፍሉበት ወቅት በመሆኑ ሁሉም ግብር ከፋይ በወቅቱ ግብሩን እንዲከፍል ያሣሠቡት የድሬደዋ አስተዳደር ገቢዎች…

    Read More

      የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ወገንን የመርዳት ባህል እንድናዳብር አቅም ፈጥሮልናል -ወጣቶች

      በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በመላ ሀገሪቱ ከ10-ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር 60ሺ ወጣቶች ይሳተፋሉ፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውንና ሃብታቸውን በማስተባበር ወገንን የመርዳት ባህል እንዲያዳብሩ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን ወጣቶች ገለፁ፡፡ ባለፈው ቅዳሜ በችግኝ ተከላ ስነ ስርዓት የተጀመረው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በያዝነው ክረምት ከ60ሺህ በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሰማራታቸውን የአስተዳደሩ…

      Read More

        የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ11ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2ሺ 800 ተማሪዎች አስመረቀ

        የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የቀሰሙትን እውቀት በመጠቀም ለሀገር እድገትና ብልጽግና እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡        ዩኒቨርሲቲው በ6 ኮሌጆችና በ41 የትምህርት ክፍሎች ተቀብሎ ያሰለጠናቸውን 2ሺ 800 ተማሪዎች ለ11ኛ ጊዜ በድምቀት አስመርቋል፡፡ በዚሁ ስነ ስርአት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በሚኒስቴር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ስረአት ግንባታ መአከል አስተባባሪ የዩኒቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ…

        Read More

          የክረምት በጎ ፍቃድ ስራው በይፋ ተጀምሯል  በበጎ ፍቃድ ስራው – 60 ሺ ወጣቶች ይሳተፋሉ፡፡ ከ55 ሚሊየን ብር በላይ ማትረፍ ይቻላል፡፡

               በዘንድሮ አመት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ጥሪ መሰረት በአገር አቀፍ ደረጃ 4ሚሊየን ያህል ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል፡፡ ከዚህም ውስጥ አስተዳደራችን ድሬዳዋ 250 ሺ ያህሉን ችግኞች በመትከል የድርሻዋን ሚና ለመወጣት ዱላ ቅብብሎሹን ጀምራለች፡፡        በመላው አለም ከአየር ብክለት ጋር በተያያዘ በሚከሰቱ የካንሰርና የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች በየአመቱ 7 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ወይም…

          Read More

            አመለ ሸጋው አሰግድ ተስፋዬ ታስቦ ውሏል

            በእግር ኳስ ሂወቱ በርካቶችን ያስደመመው አሰግድ ተስፋዬ ( ፔሌ ) ሁለተኛ  ሙት ዓመት መታሰቢያ በእግር ኳስ ጨዋታ ዝግጅት ተከብሯል፡፡ የአሰግድ ተስፋዬ ሁለኛ ዓመት ታስቦ ሲውል በርካቶች አሁንም ድረስ ከአይምሮአቸው የማይጠፋውን የእግር ኳስ ችሎታውን በማስታወስ ነበር፡፡ አመለሸጋው አሰግድ ተስፋዬ ከእግር ኳስ ችሎታው በተጨማሪ በስፖርታዊ ጨዋነት ለበርካታ ተጫዋቾች አርያ መሆን የቻለ ነው፡፡ ዛሬም ድረስ ህልፈቱ ለበርካቶች አስደንጋጭ…

            Read More

              የኦሎምፒክ ሳምንት የጎዳና የሩጫ ውድድር

              የኦሎምፒዝም የሰፖርት መረሆዎችን አላማ ታሳቢ በማድረግ የሚከበረው የኦሎምፒክ ሳምንት በከተማችን ድሬደዋ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ተከበሯል፡፡ ከነዚህ መርሀ ግብሮች መካከል የ5 ክሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ሳምንቱን አድምቆታል፡፡ ለወደፊት እሮጣለሁ በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ከህፃናት እስከ አዋቂዎች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያካፈለ ነበር፡፡   የአለም የኦሎምፒክ ሳምንት በዚህ ደማቅ የሩጫ ውድድር…

              Read More

                የኦሎምፒክ ሳምንት በድሬዳዋ በከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ እየተከበረ ነው

                     ለአለም አቀፍ መድረኮች አገራችን ኢትዮጵያ ያስጠሩ እና ሰንደቅ አላማችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደረጉ አትሌቶች አሉን፡፡        እነዚህ አትሌቶች እና በአለም አቀፍ መድረክ ያለን ገናና ዝና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለኦሎምፒክ ስፖርት እና ለኦሎምፒዝም ትልቅ ትኩረት በመስጠት በአገር አቀፍ ደረጃ ንቅናቄ ይደረጋል፡፡      በከተማችን ድሬዳዋም ኦሎምፒክ ሳምንት በከፍተኛ ህዝባዊ ተሳትፎ እና ንቅናቄ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡…

                Read More

                  ህብረተሰቡ ደረሰኝ የመጠየቅ ባህሉን በማዳበር የአገሪቷን ገቢ በማሳደግ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

                  «ግዴታዬን እወጣለሁ መብቴን እጠይቃለሁ»  በሚል መሪ ቃል ከግንቦት 18 እስከ ሰኔ 16/2011 ዓ.ም ለአንድ ወር በተለያዩ ዝግጅቶች በአስተዳደሩ የተከበረው የታክስ ንቅናቄ ውጤታማ እንደነበር ተገለፀ፡፡   በድሬደዋ አስተዳደር የገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሊድ መሀመድ ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የታክስና የገቢ ንቅናቄ፣ በስፖርታዊ ውድድሮች፣ በፓናል ውይይቶች እንዲሁም በመስክ ጉብኝቶች መከበሩን ገልፀዋል፡፡ የታክስ ንቅናቄው ለአንድ ጊዜ ብቻ…

                  Read More

                    መጪውን ክረምት ከመፃህፍት ጋር ለማሳለፍ የሚያግዝ የንባብ ሣምንት ተከበረ  የማይጠቅም ባህልን በማስወገድ፣ የሚበጀንን በማስቀጠል፣ መልካምን መልመድ ይገባል ተብሏል፡፡

                    የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፃሐፍት ኤጀንሲ ከድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት እንዲሁም ከድሬዳዋ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን የተዘጋጀው “ክረም  ተ መፃህፍት በአንባቢዋ ድሬ” የንባብ ሣምንት በተለያዩ ዝግጅቶች ታዋቂ ደራሲያንና የኪነ-ጥበብ ሰዎች በታደሙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል፡፡ አውደ ርዕዩ በድሬዳዋ አስተዳደር ሲከበር ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡   ባሳለፍነው ሳምንት በአስተዳደራችን ድሬዳዋ ምድር ባቡር…

                    Read More

                      ህብረተሰቡን ያማከለ መሠረተ ልማት ለመዘርጋት ፍላጐትን አካቶ ማቀድ እንደሚገባ ተገለፀ

                        ከ2012 እስከ 2014 ዓ.ም የካፒታል ኢንቨስትመንት እቅድን ለማካሄድ በአስተዳደሩ ባሉ ቀበሌዎች ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሴቶችና ወንዶች  እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን አሳታፊ ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተሠጥቷል፡፡ የከተሞችን የመሠረተ ልማት የማስፋፋት አቅም ለማጠናከርና በከተሞች  መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተሞች ተመርጠው የበጀት ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ ድጋፍ አማካኝነትም ባለፉት ዓመታት በርካታ የመሠረተ…

                      Read More