በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 5ተኛ አገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡
በአገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ “የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ሁሉን አቀፍ ለሆነ እድገት፡፡” በሚል መሪ ቃል ለሁለት ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄዷል፡፡ በኮንፈረንሱ የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ እንደተናገሩት እንደዚህ አይነት ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ መካሄድ ልምድ ለመለዋወጥ ዋና ድልድይ ነው ብለዋል፡፡ እንደ ዶ/ር ያሬድ ማሞ ገለፃ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማርና የምርምር ስራዎችን…


