አገራዊ ሪፎርም ለጠንካራ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል 15ተኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የፓናል ውይይት ተካሄደ።
የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ እንዲሁም የመክፈቻ ንግግር በማድረግ መድረኩን የከፈቱት የድሬዳዋ አስተዳደር አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የሀገር መከላከያ ሠራዊታች መቀሌን ከጁንታው ነጻ ባደረገበት ማግስት በመገናኘታችን እንኳን አደረሰን መልዕክታቸውን በማስተላለፍ የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ሰራተኞች ከዚህ በፊት በአስተዳደራችን ከቻርተር ምስረታ ከተማው እንዳያድግ እንቅፋት የሆነባት ቢሆንም ከለውጥ ማግስት ቻርተሩን በመከለስ ችግሩ በዘላቂነት ይቀረፋል ብለዋል።
የፓናል ሰነዱን በድሬዳዋ አስተዳደር የስራ የአመራር እና የካይዘን ኢንስቲትዩት ኃላፊ አቶ አወቀ ለገሰ ”ነፃ ገለልተኛና ብቃት ያላቸው ተቋማት ግንባታ እንደ ወሳኝ የሪፎርም አጀንዳ” እንዲሁም በድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ ደራራ ኢብራሂም ”የህወሃት ኢ-ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴና ፌዴራላዊ ስርዓቱን ለማዳን የተደረጉ ጥረቶች” ቀርቧል።
በቀረበው ፅሁፍ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ እና የድሬዳዋ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ ሰፊ ውይይት በማድረግ አጠናቀቁ።


