15ኛዉ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በ06 ቀበሌ በፓናል ውይይት ተከብሯል::

    በቀበሌ 06 አስተዳደር “ኢትዮጵያ ብሔርብሔረሰቦችና ህዝቦች አንድነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ለ15 ኛዉ ጊዜ የሚከበረዉን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በሴት አደረጃጀቶችና ወጣቶች የአካባቢዉ ነዋሪዎች የፓናል ዉይይትና ለመከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስ ተከብሮ ውሏል ፡፡
    በቀበሌዉ አመራሮች የህወዋትና ኢ-ህገመንግስት ሰነድ፣ሀገራዊ ሪፎርም ለጠንካራ ሀገራዊ ፌዴራላዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ በሚል ርዕስ ሰነዶች ቀርበዋል፡፡
    በፓናል ዉይይቱም ላይ የተሳተፉ ተሳታፊዎችም በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብና አስተያየት የሰጡ ሲሆን የሴቶች ተጠቃሚነትን ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በማመላከት ጁንታዉ የህዉዋት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ማድረሱ እንዳሳዘናቸው በመግለፅ መንግስት እየወሰደ ያለዉ እርምጃ ተገቢ ነዉም ብሎዋል፡፡
    ተሳታፊዎቹ አክለዉም ህወዋት ክልልን ከክልል ፣ ብሄርን ከብሄር፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት ወጣቶችን የራሳቸዉን ስራ እንዳይሰሩ በእኩይ ስነ -ምግባር በጥቅም በማታለል የወጣቶችን አዕምሮ በርዞዋል በቀጣይ ይህንን ከአዕምሮዋችን በማጥፋት በሰፈር የተጣሉትም እርቅን በመፍጠር ሰላምን ማስፈን እንዳለባቸው በመወያየት ህይወታቸዉን ሰዉተዉ የኛን ሰላም እያስጠበቁ ላሉት ለጀግናዉ የመከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል፡፡
    ምንጭ፡-የ06 ቀበሌ አስተዳደር ኮሚኒኬሽንና ህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ