የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ለአስተዳደሩ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ::

    የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ከአለም ባንክ /WORLD BANK/ ጋር በመተባበር ለህዝብ ቅሬታ ሰሚ እና አጋር አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።
    በስልጠናው የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ተግባርና ኃላፊነት፣ ደንብና መመሪያ፣ የመረጃ ነጻነት አዋጅ እንዲሁም ስለቅሬታ አቀራረብና አፈታት መመሪያ የቀረበ ሲሆን በሰነዶቹ ዙሪያ የነበረው ግንዛቤና ከዚህ ቀደም ሲያጋጥሙ የነበሩ ክፍተቶች ተዳሰዋል።
    የቅሬታ አቀራረብ ስርዓቱ በአካል ማቅረብ ለማይችሉ አካላት እንዲሁም አቀራረቡን ለማዘመን የቅሬታ መቀበያ የጥሪ ማዕከል በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገልጿል።
    በመጨረሻም በቀረቡ ሰነዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ በቀጣይ ትኩረትና ርብርብ በሚፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመያዝ ተችሏል።