የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት በህዳር ወር የመንግስት ግብር 96.39% እቅዱን ማሳካቱን እና በአምስት ወራት ውስጥ ከ581 ሚሊዬን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልፇል።

    የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሐመድ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም አስመልክተው አጭር መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
    ባለስልጣን መ/ቤቱ በ2013 በጀት ዓመት በአምስት ወር ከመንግስት ታክስ እና ከመዘጋጃቤታዊ ገቢ ብር 746,686,895.38 ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 581,401,743.19 መሰብሰብ የቻለ ሲሆን ክንውኑ ከዕቅዱ ጋር ሲነፃፀር 77.86በመቶ አፈፃፀም አለው፡፡
    ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የ2013 በጀት ዓመት የአምስት ወራት አፈፃፀም ከ2012 ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በ7.68በመቶ ወይም በብር 41,450,318.19 ብልጫ እንዳለው በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡
    እያንዳንዱን የገቢ አይነት ነጣጥለን ሰንመለከት የመንግስት ታከስ ብር 547,001,908.04 ለመሰብሰብ ታቅዶ 519,895,678.06 በመሰብሰብ የዕቅዱን 95.04በመቶ ማሳካት ተችላሏ፡፡ ይህ ዕቅድ አፈፃፀም ከ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 11.17በመቶ ወይም በብር 522,550,018.22 ብልጫ አለው፡፡
    የማዘጋጃቤታዊ ገቢን ስንመለከት በአምስት ወር ውስጥ ብር 199,686,895.38 ለመሰብሰብ ታቅዶ 61,506,065.13 በመሰብሰብ የዕቅዱን 0.31በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡ ይህ አፈፃፀም ከባለፈው 2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 14.94በመቶ ወይም በ10,804,700.03 ብር ያንሳል፡፡
    ባለስልጣን መ/ቤቱ በ2012 በጀት ዓመት ላስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት የባለስልጣን መ/ቤቱ ሰራተኞችና አመራሮችን እውቅና ሰጥቷል።
    ምንጭ የድሬደዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን