ወጣቶቹ በራሳቸው ተነሳሽነት እያደረጉት ካለው የአካባቢ ሰላም የመጠበቅ የሮንድ ጥበቃ ስራ ባሻገር በዛሬው እለት ከቀበሌ እና ከቀጠናው ፖሊስ አመራርና አባላት ጋር በመሆን በቤተ እምነቶች ተገኝተው የፅዳት ዘመቻ አካሂደዋል።
በዚሁ የፅዳት ዘመቻ ላይ በመገኘት ቅድሚያ መልዕክት የሳተላለፉት የድሬደዋ ፖሊስ ኮምሽን የወ/ል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጉሌድ ድርዬ “ወጣቶች ለሀገር ልማትና ብልፅግና ሚናችሁ የላቀ እንደመሆኑ ከጥፋት ሀይሎች እኩይ ተግባር በመራቅና የአካባቢያችሁን ሰላም በመጠበቅ ሀገርዊና አካባቢያዊ ሀላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል” ካሉ በሃላ ወጣቶቹ ከአካባቢ የሮንድ ጥበቃ ጋር በተያያዘ እየሰሩት ላለው ፀጥታን የማስከበር ስራ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::
በዚሁ በቀበሌው በሚገኙ ቤተ እምነቶች የፅዳት መርሀ ግብር የአስተዳደሩ የፍ/ፀ/ህ/ጉ/ ምክትል ቢሮ ህላፊ የአቶ አብደላ በከር ና የቀበሌው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አዩብ ኢብራሂም ባደተጉት ንግግር ወጣቶቹ እያካሄዱት ያለው ተግባር የሚበረታታ እንደመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተገቢው ድጋፍ ይደረጋል ያሉ ሲሆን የለገሀሬ ፖ/ጣቢያ ሃላፊ ዋ/ኢ/ር አብዱሳ ቁሴ በበኩላቸው ከወንጀል ነፃ የሆነ አካባቢን ለመፍጠር ወጣቶችንና ሌሎች የህ/ብ ክፍሎችን ባቀፈ መልክ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል::
በቤተ እምነቶች ተገኝተው የፅዳት ዘመቻውን ያደረጉት ወጣቶች በበኩላቸው ያካሄዱት የፅዳት ዘመቻ የወጣቶቹን አንድነትና አብሮነት ያሳ እንደሆነና በዚህን ባከናወኑት ተግባር ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል::
ወጣቶቹ አያይዘውም ያለባቸውን ማህበረሰባዊ ሀላፊነት ለመወጣት የጀመሩትን የአከባቢን ሰላም የማረጋገጥ የሮንድ ተግባር አጠናክሮ የመቀጠል እንዲሁም መጪው የጥምቀተ በዓል በሠላም እንዲከበር የማስቻል ስራዎችን ይበልጥ በአንድነት ከፖሊስና ከቀበሌው ፀጥታ ዘርፍ ጋር እየሰሩ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል::
ወጣቶቹ በዛሬው እለት ከለገሀሬ ቀበሌና የቀጠናው ፖሊስ ጣቢያ አመራርና አባላት ጋር በመሆን በቀበሌው በሚገኙት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ እና በሼክ አብዱረህማን ዳሞታ መስኪድ ነው የፅዳት ዘመቻውን ያካሂሄዱት::
ምንጭ ድሬ ፖሊስ


