የአስተዳደሩ የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ በውድድሩ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት ውድድሩ በከተማችን መካሄዱ በቅርጨት ኳስ ስፖርት የጀመርናቸውን እንቅስቃሴዋች ለማጠናከርና ወጣቶችን ለማነቃቃት ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።
ኮሚሽነር ሻኪር አክለውም ተሳታፊዎች በድሬዳዋ ቆይታቸው እንደሚደሰቱ በመጠቆም ለእንግዶቹ በቆይታቸው ሕብረተሰቡ የተለመደውን የእንግዳ ተቀባይነት ባህሉን እንደሚያሳያቸው እምነቴ ነው ብለዋል።
በውድድሩ ላይ ስምንት ቡድኖች በሁለቱም ፆታ የተሳተፉ ሲሆን በመክፈቻ ጨዋታውም በሴቶች የአማራ መንገድና ህንፃ ዲዛይን አማካሪ ከሐዋሳ ተጫውተዋል።
ድሬዳዋ ከተማ የቅርጫት ኳስ የወንዶች ቡድን ተጋጣሚያቸውን ጎንደር ከተማን 77 ለ 38 አሸንፎል፡፡ሌሎች ጨዋታዎችም ተካሄዷል ፡፡
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ በድሬዳዋ የሚገኙ የሙዚቃ ቡድኖች ባህላዊ ትሪይት የመክፈቻ ስነ ስርአቱን ደማቅ አድርጎታል።
ውድድሩ በነገው እለትም ጠዋት 2:00 ሰዓት ጀምሮ በኮሚሽኑ ሁለገብ ሜዳ ይካሄዳል፡፡
የጥር 17/2013ዓ.ም የውድድር ኘሮግራም
በሴቶች ….ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከአዋሳ ከተማ
በሴቶች …… ጅማ ከተማ ከአማራ መንገድና ህንፃ ዲዛይን
ወንዶች…….. የካ ክፍለ ከተማ ከጎንደር ከተማ
ወንዶች…….. ወልቂጤ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ


