በ8ኛው ሀገር አቀፍ የቅርጫት ኳስ ክለቦች ኘሪምየር ሊግ ውድድር ለተሳታፊዎች ልዑካን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሲዘጋጅ ዛሬ በድሬዳዋ ዩንቨርሲቲ ምሁራን በቀረበው መነሻ ጽሁፍ በስነ ልቦና እና የ2020 አለም አቀፍ የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ህጎች ማብራሪያና ትርጉም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለልዑካን ቡድን አባላት ስልጠናው መሰጠቱን የኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ኢብሳ ዱሪ ገልፀዋል ፡፡
እንደ ባለሙያው አቶ ኢብሳ ገለፃ በተዘጋጀው ስልጠናው ላይ ከተለያዩ አካላት አሰልጣኞች ፡ዳኞች ፡ ኮሚሽነሮችና የስፖርት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ፡፡
በሌላም በኩል….ነገ ጥር 16ቀን 2013 በድሬዳዋ አስተናጋጅነት ከጠዋት 2:00 ሰዓት ጀምሮ በኮሚሽኑ ሁለገብ ሜዳ በሚጀመረው የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ኘሪምር ሊግ ክለቦች 1ኛው ዙር ውድድር 5 የወንድና 5 የሴቶች ክለቦች የሚካፈሉ ሲሆን እስከ ጥር 22/2013 ይካሄዳል፡፡


