በድሬዳዋ የኢትዮጵያ የቅርጫት ኳስ ክለቦች ኘሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ለማዘጋጀት የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ኮሙሺነር ሻኪር አህመድ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል።
ኮሙሺነር ሻኪር ከዚህም ጋር አያይዘው 8ኛ ሀገር አቀፍ የቅርጫት ኳስ ክለቦች ኘሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ነገ ጠዋት በኮሚሽኑ ሁለገብ ሜዳ ይካሄዳል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የቅርጫት ኳስ ክለቦች ኘሪምየር ሊግ ሻምፒዮን የ1ኛው ዙር ውድድር ከነገ ጥር 16 ቀን እስከ 22/2013 እንደሚካሄድ የገለፀት ኮሚሽነር ሻኪር በሻምፒዮናው በሁለት ምድብ በወንዶች 6 : በሴቶች 6 ቡድኖች መካከል ውድድሩ ይካሄዳል ብለዋል።
ኮሚሽነር ሻኪር ለአስተዳደሩ ነዋሪዋች ባስተላለፉት መልዕክት ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሳታፊ ክለቦችና እንግዶችን የድሬዳዋ እሴት በሆነው የአብሮነት፣ የፍቅርና የእንግዳ ተቀባይነትን ባህላችንን በማሳየት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪአቸውን አቅርበዋል ፡፡
የኮሮና ቫይረስን በውድድሩ ለመከላከል የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ እንዲጠቀሙ፣አካላዊ ርቀትና ፤የእጅ ንጽሕና እንዲጠብቁ የቅድመ ዠግጅት ስራ መሰራቱን ኮሚሽነር ሻኪር ጠቁመዋል።


