በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት በአንድ ሕንፃ ላይ የእሳት ቃጠሎ ተከስቷል፡፡

    በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ገደማ በአንድ ህንፃ ላይ በሚገኝ የዕቃ ግምጃ ቤት ውስጥ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ ንብረት የጠፋ ሲሆን በአደጋው የአንዲት የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ የሆነ የዘጠኝ አመት ህፃን ልጅ ህይወት ማለፉ ታውቋል።ዩኒቨርሲቲው በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ እና ዘመዶቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
    የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት ፖሊስ የምርመራ ስራ የጀመረ ሲሆን ፖሊስ የደረሰበትን ውጤት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ እና የእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ የፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራን፣ ሰራተኞች እና ተማሪዎች ላደረጋችሁት ጥረት ዩኒቨርሲቲው ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል፡፡
    ምንጭ ድሬደዋ ዩኒቨርስቲ